ጠ/ሚ ዐቢይ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

መስከረም 27/2014 (ዋልታ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጋር  በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም በጋራ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የኤሚሬት ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በድጋሚ በመመረጣቸውም የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡