ጠ/ሚ ዐቢይ ከኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያዩ

መጋቢት 22/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ እና በባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸውን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ኢትዮጵያ ከኮሞሮስ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል፡፡
እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ለማጠናከርም ትሠራለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።