ጠ/ሚ ዐቢይ ከጂቡቲው ፕሬዝዳንት ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጂቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

የጂቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ፕሬዝዳንቱ ዛሬ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ የሁለቱ አገራት መሪዎች በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም እንደገለጹት መሪዎቹ በዋናነት ኢትዮጵያና ጂቡቲ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም ቀጣናዊ ትስስር ስለሚጠናከርበት ሁኔታም መምከራቸውን ገልጸዋል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!