ጠ/ሚ ዐቢይ የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማኅበረሰቡን ጎበኙ

ጠ/ሚ ዐቢይ

ሚያዝያ 15/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማኅበረሰቡን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትርሩ ከማኅበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀዋል።

እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ አመልክተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚስተዋለውን የግጭት ሁኔታ አንስተው ሰላምን ማስፈን የሰላማዊ ወኪል ለመሆን ወስኖ በቁርጠኝነት የሰላም እሴቶችን መገንባትን ይጠይቃል ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW