ጠ/ሚ ዐቢይ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉት ምስጋና አቀረቡ

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒሰቴር አብይ አህመድ የኢሬቻ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጾ ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የ2014 ዓ.ም ኢሬቻ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አክብረናል። ኢሬቻ የምስጋና ፣ የዕርቅ እና የሰላም በዓል ነው። የፍቅር ፣ የይቅርታ እና የአንድነት በዓሉን በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋፅኦ ያደረጋችሁትን ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ሲሉ አስፍረዋል፡፡