ሚያዚያ 08/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የተላከውንና በአምባሳደር ክዋሜ ታፒዋ ሙዛዋዚ የሚመራውን ልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ልዑካኑ ያለፉት 500 ዓመታት የአፍሪካ ትክክለኛው ታሪክ እንዲመዘገብ የአፍሪካ ሕብረት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት፥ የተዘጋጀውን “አፍሪካን ፋክት ቡክ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ አበርክተውላቸዋል።
የአጀንዳ 2063 እጅግ ጠቃሚ አካል የሆነው ይህ የእውነታዎች ስብስብ፣ የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክና ትውፊት ለዓለም የሚያስተዋውቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ልዑካኑ ይህንን መጽሐፍ በማበርከት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነት የተጫወተችውን አይተኬ ሚና እና ለፓን-አፍሪካዊነት የምታደርገውን ቀጣይ ድጋፍ በማድነቅ ዕውቅና መስጠታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።