ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን መትከል ያስፈልጋል – ዶ/ር አለሙ ስሜ

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – አገር አቀፍ የሴቶች ችግኝ የመትከል ማሰጀመርያ መርሀ ግብር በአማራ ክልላዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባንጃ ወረዳ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ የፖለቲካ ፖርቲዎችና ሲቪል ማህበራት ዘርፍ ሚኒስትር፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ፣ የሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ መሰረት መስቀሌና እና ሌሎች የመንግስት የስራ አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል።

ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን የማልበስ ስርዓትጉዞ ጀምረናል ያሉት ዶ/ር አለሙ ስሜ አረንጓዴ የለበሰች ሀገር ለትውልድ ለማሳለፍ የሴቶች ሚና ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ጥላቻን መንቀልና ኢትዮጵያን መትከል አላማ አድርጎ የተነሳ መሆኑን አንስተዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ብቻ ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን በውስጥ ጉዳይ አንድነትን በማጠናከር በፖለቲካው ዘርፍ ድል መንሳቱን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እማኝ ነው ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በዘመናት ብዛት የማይደበዝዝ የአንድነት አሻራ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ያሉት።

የሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስትር ዴኤታ መሰረት መስቀሌ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የህዝባዊ ወሳኝነትን ያረጋገጠና ንቁ ተሳትፎ የታየበትና የሴቶች ተሳትፎ የበረከተበት እንደነበር አንስተዋል።

ታላላቅ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ሰላምን በቀጣይነት ለማረጋገጥ የዲሞክራሲ ግንባታ ሴቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉ ሲሆን የሴቶች ሁለንተናዊ መብቶችን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናለብሳለን እህትማማችነትን እናለብሳለን በሚል መሪ ሀሳብ ሀገሪቱን ለምና ለሰው ልጅ ምቹ በማድረግ እንዲሁም በረሀማነት እንዳይስፋፋ ለማድረግ ያለመ ነው።
(በዙፋን አምባቸው)