ጥላቻ፣ ኢ-ፍትሐዊነትና አመጸኝነት ለትውልድ የሚተላለፉ ክፉ ዘሮች በመሆናቸው መገታት ይገባቸዋል – ፓስተር ጻድቁ አብዶ

ፓስተር ጻድቁ አብዶ

ሚያዝያ 15/2014 (ዋልታ) ቂም በቀል፣ ጥላቻ፣ ኢ-ፍትሃዊነት፣ አመጸኝነት እና አድመኝነት ለትውልድ የሚተላለፉ ክፉ ዘሮች በመሆናቸው መጸየፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ገለጹ፡፡

ፓስተር ጻድቁ ለኢፕድ እንደለገጹት ይህንን መርገም ለማስወገድ ትክክለኛው መንገድ የሰላም፣ እርቅ፣ ይቅርታና ምህረት መንገድ ነው።

ከጥላቻ በመላቀቅ፣ ከቂም በቀል ፍላጎት በመጽዳት በአገር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በውስጣችን ካለው ክፉ ሃሳብ መላቀቅ ይገባናል ሲሉም አክለዋል።

በአገር ሰላም እንዲሰፍን መጸለይ ይገባናል፤ በተለያየ እምነት ያለን ኢትዮጵያዊያን ሃይማኖተኛ ናቸው የሚባለውን ዛሬ በተግባር መግለጽ ይገባናል ያሉት ፓስተር ጻድቁ በክርስትና፣ በእስልምናና ሌሎች እምነቶች ሁሉም መጽሐፍት ጥላቻን አያስተምሩም፣ ቂም በቀልን ለእግዚአብሔር ተው እንደሚል እንደቃሉ መታዘዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

መዘዙ ለልጅ ልጆችና ለትውልድ ስለሚተርፍ ከዚህ መንገድ መመለስ ያስፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW