የካቲት 18፣ 2013 (ዋልታ) – ጨፌ ኦሮሚያ 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ ስራዎችን መርምሮ እንመዲያጸድቅ የጨፌው አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡
ከየካቲት 17 እስከ 21 በሚካሄደው ጉባኤ ጨፌው ሰባት ረቂቅ አዋጆች ላይ እንዲሁም የሚቀርብ ሹመት ላይ ተዋያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተያዘው በጀት ዓመት ከ90 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፅድቆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ክልሉ ባለፋት 6 ወራት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ጨፌውም እነዚህን ስራዎች ለመገምገም የመስክ ምልከታ ማድረጉን ና በየ3 ወሩ የክትትልና ግምገማ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ወ/ሮ ሎሚ አንስተዋል፡፡
አፈጉባኤዋ ባለፉት 6 ወራት ሊሰራ ከታቀደው አንፃር መልካም ጅምሮች ቢኖሩም እየጨመረ የመጣውን የህበረተሰቡን ፍላጎት ከማርካት አንፃር በይበልጥ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የጨፌው መደበኛ ጉባኤ በአድዋ ድል በዓል ዋዜማ የሚካሄድ እንደመሆኑ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)