ጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ መጀበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

ሰዓዳ አብዱርህማን

የካቲት 10/2015 (ዋልታ) ጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን 2ኛ ዓመት 4ኛ መጀበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱርህማን የክልሉ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት የክልሉን ህዝብ የልማት ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉ ስራዎች ማከናወኑን አንስተዋል።

በተለይም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው አሁንም ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩና ባለሀብቶች እንዲሁም የጨፌው አባላት በያሉበት አከባቢ ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የክልሉን ህዝብ በምግብ ራስን ለማስቻል አበረታች ስራዎች በበጀት ዓመቱ አጋማሽ መሰራቱን ጠቅሰው ከነዚህም የበጋ ስንዴ ልማት ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለጨፌ ባቀረቡት ሪፖርት በክልሉ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ከተሰሩ የልማት ስራዎች የተሻለ ስኬት በማስመዝገብ ውስጥ የህዝቡ ተሳትፎ ትልቅ እንደነበር ገልጸዋል።

የህዝቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና ከራስ አልፎ ለገበያ ሊተርፉ የሚችሉ የልማት ስራዎችን በመስራት በኩል የህዝብ ተሳትፍ ከፍተኛ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

ሚልኪያስ አዱኛ (ከአዳማ)