ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) “ጳጉሜን በመደመር” በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ መከበር ጀመረ።
በዚህም ከማለዳ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች አካባቢን ማጽዳት፣ ችግኝ ተከላና የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃለፊዎችም ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ተገኝተው የበጎ ፍቃድ ቀንን አካባቢን በማጽዳት ማስጀመራቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ዛሬ ዓመቱን ሙሉ በበጎነት ስናከናውን የቆየነውን ተግባር የምናጠናቅቅበት ዕለት ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዕለቱ ከሁሉም በላይ አሸባሪው ህወሓት በከፈተብን ጦርነት ለኛ መኖር፣ ለኛ ሰላም እና ለሉአላዊነት ሕይወትን በመስጠት መስዋዕትነት እየከፈለ ያለውን ለመከላከያ ሰራዊታችን እንዲሁም ጥምር ጦሩ እየሰጠ ላለው በጎነት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW