ጽሕፈት ቤቱ 3ኛ ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ምስጋና አቀረበ

መጋቢት 29/2015 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሦስተኛ ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት ምስጋና አቀረበ፡፡

ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ በሦስተኛው ዙር ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን ዝርዝርና ገቢ ያደረጓቸውን የድጋፍ መጠን ይፋ አድርጓል።

በዚህም አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ 267 ሚሊየን 50 ሺሕ ብር፣ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ 50 ሚሊየን ብር፣ ሰይድ ያሲን ኃ.የተ. የግል ኩባንያ 10 ሚሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር 12 ሚሊየን 707 ሺሕ 692 ብር፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት 10 ሚሊየን 681 ሺሕ 559 ብር፣ ታፍ ኦይል 10 ሚሊየን ብር፣ አምደሁን ጀነራል ትሬዲንግ 10 ሚሊየን ብር፣ ኤም ደብልዩ ኤስ ትሬዲንግ 10 ሚሊየን ብር፣ ኤም ሲ ጂ ኮንስትራክሽን 10 ሚሊየን ብር እንዲሁም ጎልድ ውሃ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡