“ጽንፈኝነት የሰው ልጆች ጸር ነው” በሚል በሰበታ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) “ጽንፈኝነት የሰው ልጆች ጸር ነው” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት በሰበታ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ ከ1ሺሕ 300 የሚበልጡ የከተማዋ ወጣቶች፣ ምሁራን እና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አልፊያ አብዱረህማን የውይይቱ ዋና ዓላማ ወጣቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማስቻልና በሀገራዊ ሠላምና ጸጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ ነው ብለዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ወጣቶቹን፣ ምሁራኑን እና የንግዱን ማኅበረሰብ ተወካዮች ያወያዩ ሲሆን ሀገራዊ ለውጡን ከማረጋገጥ ረገድ ወጣቶች በነበራቸው ሚና፣ ከለውጡ ጋር ተያይዞ እየታዩ ባሉ ተግዳሮቶችና በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

በቀረበው የመነሻ ጽሑፍም ውይይት እንደሚካሄድ የኦቢኤን ዘገባ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW