ፈርስት ሂጅራ ልዩ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) ኢንተርናሽናል ፈርስት ሂጅራ ሃላል ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንት እና ቢዝነስ ኤክስፖ ከሚያዚያ 19 እስከ 23 በወዳጅነት ፓርክ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
እንዲሁም ግንቦት 6 እና 7 ዝክረ ነጃሺ ሽልማት፣ ዝክረ ነጃሺ ትያትር እና ፈርስት ሂጅራ የሩጫ እና እርምጃ ፌስቲቫል አእንደሚደረግ ነው የተገለጸው።
ዳራ ሚዲያና ኢቨንትስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበር የመጀመሪያው ፌስቲቫል እንደሚከናወን አዘጋጆቹ በቢላል ሐበሺ ማዕከል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በሰለሞን በየነ