ፋሲል ከነማ መሪነቱን አጠናከረ

 

በ11ኛ ሳምንት ቤቲኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዘገበ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ላይ ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በፋሲል ሁለት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በዛብህ መለዮ በመጀመርያው የጨዋታ አጋማሽ 45ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመርያዋን ግብ ሲያስቆጥር

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ10ጨዋታ 25ነጥብ በመያዝ ከተከታዩ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል፡፡

በሌላ ጨዋታ ዛሬ ረፋድ ላይ ወልቂጤ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡

የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት የኢትዮጵ ቡናው አቡበከር ናስር በ14 ግብ ሲመራ ፡ ሙጂብ ቃሲም ከፋሲል ከነማ በ12 ጌታነህ ከበደ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ7 ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡
(በሀብታሙ ገደቤ)