ፌዴሬሽኑ ከጀርመኑ ጂአይዜድ ጋር የ10 ሚሊየን ብር ስምምነት ተፈራመ

የካቲት 30/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ የልማት ተቋም ጂአይዜድ (GIZ) ጋር የካፍ የልህቀት ማዕከል የመጫወቻ እና ልምምድ ሜዳን ደረጃ ለማሻሻል እንዲሁም አዲስ ተጨማሪ ሜዳ ለመሥራት የሚያስችል የ10 ሚሊየን ብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት ጂአይዜድ በካፍ የልህቀት ማዕከል የሚገኘውን የመጫወቻ ሜዳ ደረጃውን የጠበቀ መልኩ የመልሶ ግንባታ ሥራ እንደሚያከናውንና አንድ ተጨማሪ አዲስ ሜዳ ደግሞ እንደሚገነባ ከፌዴሬሽኑ ያገነነው መረጃ ያመለክታል።

ከመልሶ እና አዲስ ግንባታው በተጨማሪ ለጥገና እና እንክብካቤ ሠራተኞች የሚሰጠው ስልጠናም የስምምነቱ አካል ነው ተብሏል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW