ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ የአረብ አምባሳደሮች ምክር ቤት አባላትንና የአረብ ሊግ አምባሳደርን አነጋገሩ

ግንቦት 26/2014 (ዋልታ) ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአረብ አምባሳደሮች ምክር ቤት አባላትንና የአረብ ሊግ አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የአምባሳደሮቹ ዲን ባደረጉት ንግግር ይህ ቡድን ከሦስት ዓመት በፊት ፕሬዚደንቷ ዘንድ ቀርቦ እንደተናገሩት ሁሉ በሚወክሏቸው አገሮችና በኢትዮጵያ መካከል በምክክርና በመግባባት ላይ የተመሰረተውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ አረብ አገራት የኢትዮጵያ ጎረቤት በመሆናቸው ኢትዮጵይ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ሁልጊዜም ፍላጎቷና ጥረቷ እንደሆነ ገልጸዋል።
የአረብ ሊግ አባል የሆኑ የአፍሪካ አገሮች ጠንካራ ድልድይ መሆናቸውን ገልፀው ማንኛውንም ጉዳይ በየቀጠናዎቻችን መፍታት ይገባል ሲሉ መናገራቸውን የፕሬዝደንት ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡