ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

ነሀሴ 07/2013 (ዋልታ) – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ተጠሪ ማዊራ ቺቲማን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸዉም ተጠሪው ድርጅት በኢትዮጵያ እያካሄደ ስላለው ሰፊ የግብርና ዘርፍን የማጠናከርና ማዘመን ሥራ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ድርጅቱ በኢትዮጵያ ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን ከመንግስት ጋር በቅርበት በመሥራት ሥራውን ለማስፋፋት ያለውንም እቅድ ገልጸዋል፡፡

ይህንን ስራ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት በመሥራት የበለጠ እንዲያስፋፋም ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዝደንቷ የግብርና ዘርፍ ለሀገራችን ዋነኛ ከሆኑት ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ የተጀመረውን ሥራ መንግስት ያወጣቸውን ግቦች ከግብ በማድረስ ረገድ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።