የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካፒቶል ሂሉን ሁከት አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ውሳኔ ተላለፈ።
የህግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን የካፒቶል ሂል ሁከት በመምራት እንዲከሰሱ በአብላጫ ድምጽ ወስነዋል፡፡
እንደራሴዎቹ 232 በ197 በሆነ አብላጫ ድምፅ ነው ፕሬዚዳንቱ እንዲከሰሱ የወሰኑት፡፡
ትራምፕ ጆ ባይደን ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስና ደጋፊዎቻቸውን ለአመፅ በማነሳሳትም በተወካዮች ምክር ቤት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎም ትራምፕ ስልጣን ላይ እያሉ ሁለት ጊዜ እንዲከሰሱ የተወሰነባቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡
ባለፈው የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ ጥቅምት 20 ቀን በይፋ በዓለ ሲመታቸው ይካሄዳል፡፡