ፕሬዚዳንት ፑቲን አገራቸው ከዩክሬን እና ከውጭ አጋሮች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ተናገሩ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ከዩክሬን እና ከውጭ አጋሮች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት አገራቸው ከዩክሬን እና ከውጭ አጋሮች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል ሲል ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስነብቧል።

11 ቀናትን ባስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አገራቱ ከትናንት በስቲያ ለሰላማዊ ዜጎች ሰብአዊ መተለለፊያ ኮሪደር ለማዘጋጀት መስማማታቸው ይታወሳል።

በአገራቱ መካካል ያለውን ጦርነት ተከትሎ የሚካሄደውም የሰላም ድርድርም ነገ ለሶስተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።