ሐምሌ 23፣ 2013 (ዋልታ) – ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ ጉዳዮች የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ ጉዳዮች USG እና የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ሆነዉ በቅርቡ የተሾሙትን ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተገናኝተዉ በትግራይ ክልል ስላለዉ የጸጥታና የሰብአዊ እርዳታ ሁኔታ ተወያይተዋል።
ግሪፊትስ የተ.መ.ድ. የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ፍላጎቶች በሚያሟላ መልኩ መስራት እንደሚፈልግና ከሀገሪቷ ጋር ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰራም አስታዉቀዋል።
ፕሬዝዳንቷ አሳሳቢ የሆኑትን ሰብአዊ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከUNOCHA ጋር ያለዉን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸውን ከፕሬዘዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።