ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን ጎበኙ

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን ጎበኙ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ለፕሬዝዳንቱና ለልዑካን ቡድናቸው አቀባበል በማድረግ የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዝብሽን እና የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ማስጎብኘታቸውን ከኢመደአ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ዛሬ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW