ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በድምፃዊ ማዲንጎ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንቷ ታዋቂው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ገና በአፍላ ዕድሜ ላይ እያለ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ በጣም ማዘናቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትንና ብርታትን እመኛለሁም ብለዋል፡፡