ሰኔ 11 / 2013 (ዋልታ) – ፕሬዘዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከተመራው የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ጋር ተወያይተዋል።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡት የምርጫ ታዛቢ ቡድኑ ከ45 በላይ አባላት አሉት።
በተመረጡ የምርጫ ጣቢያዎች በመዘዋወር ቅድመ ምርጫ፤ የምርጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ያሉትን እውነታዎች እንደሚታዘብ ቡድኑ አብራርቷል።
ፕሬዘዳንት ሣህለ ወርቅ የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ከመሆኑም በላይ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦባሳንጆን በቡድን መሪነት መመደብ አመስግነው፤ለቡድኑም መልካም የሥራ ጊዜ ተመኝተዋል።
በተጨማሪም ”ምርጫ በእራሱ ግብ አለመሆኑን፤ካለፈው እያሻሻልን እንደምንሄድ፤ለምርጫ ስኬት ብቸኛ ፎርሙላ እንደሌለ መግለጻቸውን ከፕሬዘዳንተ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በአባልነትና በመምራት በአፍሪካ ሀገሮች ምርጫ መታደማቸው አይዘነጋም።