ፕሬዝዳንት ቡሃሪ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት ለመመስረት የሚያስችልዎትን ድምጽ በማግኘትዎ በናይጄሪያ ህዝብ ስም እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

በመልዕክታቸው ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሚያግዙ አዳዲስ ፖሊሲዎችን በመተግበርና ዴሞክራሲን በመገንባት ሂደት ቁርጠኝነትን እንዲያሳዩም ማሳሰባቸውን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡