የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለጸ፡፡ፕሬዝዳንት ማክሮን የቫይረሱ ምልክቶችን ካዩ በኋላ ባደረጉት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ነው ጽህፈት ቤታቸው የገለጸው፡፡
የ42 አመቱ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ያሳዩበት የወረርሽኙ ምልክቶች ግን አልተገለፀም።
ፕሬዝዳንቱ ስራቸውን በማከናወን ከዛሬ ጀምሮ ለሰባት ቀናት ራሳቸውን እንደሚያገሉም መታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡