ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን የሚላከው እህል ወደ ድሃ ሀገራት እየተላከ አለመሆኑን ተቃወሙ

ጳጉሜ 4/2014 (ዋልታ) የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ወደ ውጭ የሚላከው እህል ወደ ድሃ እና ታዳጊ ሀገራት ሳይሆን ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት እየተላከ በመሆኑ ተቃውሟቸውን ገለጹ፡፡

በሩሲያ የፓሲፊክ ወደብ ቭላዲቮስቶክ ውስጥ በተደረገ የኢኮኖሚ መድረክ ላይ ከዩክሬን ወደ ውጭ የሚላከው እህል ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ ድሃ እና ታዳጊ ሀገራት ሳይሆን ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት ይላካል መባሉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን በተባበሩት መንግስታት በሚደገፈው በዚህ ስምምነት መሰረት የሚላከው የዩክሬን እህል ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ አውሮፓ ሀገራት እየደረሰ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ፑቲን ያቀረቡትን ተቃውሞ ውድቅ አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በየካቲት ወር ዩክሬን እንድትወረር በማዘዝ የእህል ምርቱ ላይ መስተጓጎልን አስከትሏል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ሁለቱ ሀገራት ትላልቅ የስንዴ እና ሌሎች እህል ላኪዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡