ፖላንድ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ እንደምትደግፍ አስታወቀች

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) ፖላንድ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን በተመረጡ ዘርፎች ላይ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋገጠች።

16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም በፖላንድ እስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ከፎረሙ ጎን ለጎን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ከፖላንድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲጂታል ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ክሪሺሽቶቭ ሹበርት ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትየጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ቀርፃ በግብርና፣ ቱሪዝም፣ አምራች ኢንደስትሪና በአይሲቲ ዘርፍ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰራች መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በእነዚህና በሌሎችም የዲጂታል ልማት መስኮች ዙሪያ በትብብር መስራት እንደምትፈልግም መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የዲጂታል ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ክሪሺሽቶቭ ሹበርት በበኩላቸው ሀገራቸው በዲጂታል ልማት ዙሪያ ያላትን ልምድ ለሚኒስትር ዴኤታዋ አጋርተዋል፡፡