1ሺሕ 179 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 17/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ 1ሺሕ 179 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከእነዚህ ውስጥ አንድ ህጻንና 1ሺሕ 178 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ 42 ሺሕ 90 ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል፡፡