1ሺሕ 30 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ሰኔ 1/2014 (ዋልታ) በዛሬው እለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ 1ሺሕ 30 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከተመላሾቹ ውስጥ 209 ሴቶች፣ 68 ህጻናትና 753 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ 34 ሺሕ 328 በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል፡፡