1ሺሕ 443ኛው ዓመተ ሂጂራ የኢድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 24/2014 (ዋልታ) 1 ሺሕ 443ኛው ዓመተ ሂጂራ የኢድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ስቴዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው።

“ከኢድ እስከ ኢድ” ጥሪን ተቀብለው ወደ አገራቸው የገቡ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የአዲስ አበባ እና አካባቢው ሕዝበ ሙስሊም፣ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች በአዲስ አበባ ስቴዲየም በጋራ ማክበር ጀምሯል።

ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በርካታ ሕዝበ ሙስሊም በአዲስ አበባ ስቴዲዮም በመሰባሰብ ነው በዓሉ መከበር የተጀመረው።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!