1ሺሕ 88 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺሕ 88 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ፡፡
ከተመላሾቹ ውስጥ 149 ሴቶች፣ 229 ህጻናትና 710 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ 27 ሺሕ 956 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡