1 ሺሕ 159 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ከሳኡዲ አረቢያ ተመላሾች

ሐምሌ 22/2014 (ዋልታ) በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 159 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከተመላሾቹ መካከል 1 ሺሕ 156 ወንዶች እና 3 እድሜው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው 58 ሺሕ 301 ኢትዮጵያዊያንን መመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW