1 ሺሕ 133 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 24/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺሕ 133 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ሦስት ህጻናትና 1 ሺሕ 130 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 45 ሺሕ 325 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡