1 ሺሕ 68 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎች

ግንቦት 15/2014 (ዋልታ) በዛሬው ዕለት 1 ሺሕ 68 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ አንድ ሕጻንና 1 ሺሕ 67 ወንዶች መመለሳቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ 26 ሺሕ 868 በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW