1 ሺሕ 167 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) በሦስት ዙር በተከናወነ በረራ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 167 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 338 ሴቶች 60 ህጻናትና 769 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ25 ሺሕ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡