1 ሺሕ 17 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 22/2014(ዋልታ) በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳውዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ 1 ሺሕ 17 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተመላሾቹ መካከል አምስቱ ህጻናት ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል።

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ በአጠቃላይ 44 ሺሕ 192 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።