መስከረም 16/2016 (አዲስ ዋልታ) 1 ሺሕ 498ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በድምቀት ተከበረ።
የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሼህ ጧሃ ሀሩን በቁራን ሥርዓቱን ያስጀመሩ ሲሆን መውሊድ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የአንድነት በዓል ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ ፈትሁዲን የመውሊድ በዓል ሲከበር አላህ ሀገራችን ሰላምና አንድነት እንዲጠብቅልን ዱአ በማድረግ መሆን አለበት ብለዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በዓሉ የሚከበረው “ይቅርታው ነብይ” በሚል መሪ ሃሳብ መሆኑን በማንሳት ይቅር ባይነት አብረን እንድንጓዝ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
ከነብዩ መሀመድ ይቅርታ ባይነትና ትህትናን ልንማር ይገባል ይገባል ያሉት ኃላፊዋ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የሃይማኖት አባቶች ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ምስጋና አቅርበዋል።
በበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባና የፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።
በመስከረም ቸርነት