“100 ለወገኔ” የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር

“100 ለወገኔ”

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚካሄደው “100 ለወገኔ” የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር በይፋ ተጀመረ።

መርኃግብሩ በወጣቶች ተነሳሽነት በግንባር ለሚገኘው ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በመርኃግብሩ ላይ ሁሉም በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ የገንዘብ ድጋፉ የሚደረግበት የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000430479834 መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።