‘100 ብር ለወገኔ’ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር

ይልማ ተረፈ

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) ‘100 ብር ለወገኔ’ የሚል ሀገር አቀፍ የወጣቶች ንቅናቄ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ሊያካሂድ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ይልማ ተረፈ ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ  ‘100 ብር ለወገኔ’ የተሰኘ የገቢ ማሰባሰቢያ የወጣቶች ንቅናቄ ሊካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።

ንቅናቄው ከአንድ ወጣት 100 ብር በመሰብሰብ በግንባር ላይ ላይ ለተሰለፉ የጸጥታ አካላትና በአሸባሪው ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች ለመለገስ ያለመ መሆኑን ገልጿል።

በንቅናቄው 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ወጣቶችን ለማሳተፍ የታቀደ ሲሆን፣ 180 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል።

መርሃ ግብሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊታችን ጳጉሜን 1 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።