100 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈተው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

ነሀሴ 21/2013 (ዋልታ) – ታንዛኒያን አቋርጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረግ ህገ-ወጥ ጉዞ በታንዛኒያ መንግስት ቁጥጥር ስር የዋሉ 100 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈተው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡
አቶ አለማየሁ ከተማ እና ኢንጂነር ጃቢር በተባሉ ታንዛኒያዊያ በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች ሙሉ ወጪ ተሸፍኖላቸው ነው ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ የተመለሱት።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመታለል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው እጅግ አደገኛ የሆነ ህገ ወጥ ጉዞ የሚያደርጉ ሲሆን፤ በመንገዳቸው ላይ ለርሃብ፣ ለእስር፣ ለስቃይ ብሎም ለሞት ይዳረጋሉ ብሏል በዳረ ሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ።