10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት እጩዎች ጥቆማ የካቲት 4 ይጀመራል

የካቲት 3/2014 (ዋልታ) ለአገርና ለሕዝብ አርአያነት ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያዊያንን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሠጠው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ የካቲት 4 እንደሚጀመር የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት አስታወቀ፡፡

በመምህርነት፣ ሳይንስ፣ ኪነጥበብ፣ በጎ አድራጎት፣ ቢዝነስና ሥራ ፈጠራ፣ መንግሥታዊ ተቋማት ኃላፊነት፣ ቅርስና ባህል፣ ማኅበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነት እንዲሁም ለአገሪቱ እድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጵያዊያንን በማካተት የእጩዎች ጥቆማ እስከ መጋቢት 3/2014 ዓ.ም ድረስ የሚሠጥ ይሆናል ተብሏል።

ጥቆማው በስልክ፣ በቫይቨር፣ በቴሌግራም፣ በዋትስ አፕ፣ በኢ-ሜይል እና በፖስታ እንደሚደረግ ተነግሯል።

ለአስርት ዓመታት የዘለቀው የበጎ ሰው ሽልማት ”በጎ ሰዎችን በመሸለምና እውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ይሆናል።