11ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት አውደ ርእይ የመክፈቻ ስነሥርአት እየተካሄደ ነው

11ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት አውደ ርእይ

ሚያዝያ 06/2013 (ዋልታ) – “ሙያ ሀብት ነው” በሚል መርህ ለ11ኛ ጊዜ የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት አውደ ርእይ የመክፈቻ ስነሥርአት በጃን ሜዳ እየተካሄደ ነው፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ፖሊስና እስትራቴጂ ተግባራዊነት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚግኝ በመክፈቻ ስነሥርዓቱ ወቅት ተገልጿል።

የትክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማብቂያና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማእከላት እንዲሆኑ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና እጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ገልጸዋል።

በበጀት አመቱ ለ9 ሺህ 295 ነባር እና 3 ሺህ 802 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች በአጠቃላይ 13 ሺህ 97 ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

በአውደ ርእይ ላይ bአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ይመር ከበደ እንዲሁም የኮሌጆች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዛሬ የተከፈተው አውደርዕዩ ለአምስት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

(በትዝታ መንግስቱ)