11ኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህገ መንግስት በሙሉ ድምጽ ጸደቀ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) 11ኛ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መተዳደሪያ ህገ መንግስቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ረቂቅ ህገ መንግስት ላይ የምክር ቤቱ አባላት በጥልቀት ተወያይተው የክልሉን ህገ መንግስት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በዛሬው ዕለት ተመስርቷል፡፡

ምስረታው ከአምስቱ ዞኖችና ከአንድ ልዩ ወረዳ የተወከሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አባላትንም ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ከካፋ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡