በየካ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊትና ተፈናቃይ ወገኖች 4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

ኅዳር 9/2014 (ዋልታ) የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት አስተዳደር አመራሮችና ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉ ምግብ፣ አልባሳት፣ የህፃናት አልሚ ምግብ፣ የንፅህና መጠበቂያና ሌሎች ቁሳቁስን አካቷል፡፡
በተስፋዬ አባተ