የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአስከፊ ሁኔታ መስፋፋቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ታኅሣሥ 16/2019 (ዋልታ) –  በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአስከፊ ሁኔታ እየተሰፋፋ በመሆኑን ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የጤና ሚኒስቴር አሳሳበ፡፡
ሚኒስቴሩ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ዙሪያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴዎች እና ኃላፊዎች ጋር በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አሁን ባለው መዘናጋት ምክንያት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ እንደሆነና በየጊዜው እራሱን እየቀያየረ ማኅበራዊና ምጣኔባብታዊ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለዚህም መደበኛ የመከላከያ ዘዴዎችንና ክትባትን በመውሰድ ኅብረተሰቡ ሳይታክት ተግባራዊ እንዲያደርግ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡