12ኛው ኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዐቀፍ ንግድ ትርኢት ተከፈተ

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) “የኢትዮጵያን ይግዙ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” 12ኛው ኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዐቀፍ ንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ተከፈተ።
ዓለም ዐቀፍ የንግድ ትርኢቱን የከፈቱት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ ናቸው።
ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የግሉን ዘርፍ በማጠናከር እንዲሁም ድጋፍ በመስጠት የኢኮኖሚውን ዕድገት ማረጋገጥ የሚገባ ነው።
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞች ለምጣኔ ሃብት ያላቸው አስተዋፅኦ ዘርፈ ብዙ መሆኑን ነው የገለፁት።
ከ200 በላይ የውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች መካከል የንግድ ትስስር የመፍጠር ዕቅድ ተይዟል።
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የንግድ ትርኢት ለጎብኚዎች እስከ ግንቦት 28 ክፍት ይሆናል ተብሏል።
በሰለሞን በየነ