ኢትዮ ቴሌኮም 4ጂ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት አቀረበ

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መደበኛ ኢንተርኔት ተደራሽ ባልሆነባቸው ቦታዎች ላይ በአማራጭነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል 4ጂ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት ማቅረቡን ገልጸዋል።

አገልግሎቱ ደንበኞች በመኖሪያ አካባቢያቸው 4ጂ የሞባይል ኔትወርክን በመጠቀም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በቤት ውስጥ ማግኘት የሚያስችል አማራጭ ነው ተብሏል።

በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ የሽያጭ ማዕከሎች ከአገልግሎት መስጫ ቀፎ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መጀመሩን ገልጿል።

የፊክስድ ብሮድባንድ በመኖሪያ ቤት እና በንግድ ተቋማት ባለበት እንደሚቀጥል የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።

በአግልግሎቱ 70 ሺሕ ደንበኞች በአጭር ጊዜ ለማፍራት እንደታቀደ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ 136 ከተሞች የአራተኛውን ትውልድ (4G) አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏል።