125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የካቲት 23/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች የተከበረው 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

125ኛው የአድዋ የድል በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡