126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ነው

የካቲት 23/2014 (ዋልታ) 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጣሂር መሐመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች፣ አባት አርበኞች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ እየተከበረ እንደሚገኝም አሚኮ ዘግቧል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች መነሻቸውን አርበኞች አደባባይ አድርገው በአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት ፊት ለፊት በጃንተከል ዋርካ በኩል በእልፍኝ ጊዮርጊስ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡

126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን በሑመራ ከተማም በተለያዩ ሁነቶች በደማቁ እየተከበረ ነው ተብሏል።